Select the search type
 
  • Site
  • Web
Search
እዚህ ነህ:   ቤት
Register   |  ግባ

 

የኢትዮጵያ ኤ-አገልግሎት

የመረጃና መገናኛ ቴክኖሎጂ በአለም አቀፍ ደረጃ ለሃገራት ኤሌክትሮኒካዊ የመንግስት አስተዳደር ስርዓት ግንባታ ወሳኝ መሳሪያ ነው፡፡ በዚህም መሠረት የኢ.ፌ.ድ.ሪ መንግስት በመረጃ ቴክኖሎጂ የታገዘ መንግስታዊ አገልግሎት አሰጣጥን ለማስፈን የሚያስችል ኤሌክትሮኒካዊ የአስተዳደር ስርዓት ለመገንባት በከፍተኛ ደረጃ እየሰራ ይገኛል፡፡

ይህም የአገሪቱን የልማት ስራዎችን ውጤታማነት ለማረጋገጥ እንደሚያስችልና ህዝባዊ አገልግሎቶችን ለዜጎች፣ ለነዋሪዎችና ለንግድ ማህበረሰብ አካላት ተደራሽ ለማድረግና እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ለማሻሻል እንደሚያግዝ ይታመናል። በመረጃና መገናኛ ቴክኖሎጂ በመታገዝ የቀረቡ አገልግሎቶች በአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት
፣ የዜጎችና የመንግስት ወጪን በመቆጠብ፣ የአገልግሎቶችን ተደራሽነት በማሻሻል እና የህዝባዊ አገልግሎቶችን አሰጣጥ ግልፅነትና ተጠያቂነት በማስፈን ረገድ ያላቸው አስተዋፅኦ የላቀ ነው።

የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መንግስታዊ የመገናኛን መረጃ ቴክኖሎጂ ልማት ስራዎችን የመምራት፣ የማስተባበር፣ የመከታተልና የመቆጣጠር ስልጣንና ተግባር የተሰጠው ሲሆን የተለያዩ የመንግስት አካላት ለዜጎችና የንግዱ ማህበረሰብ አካላት ኤሌክትሮኒካዊ አገልግሎት አቅርቦትን በመደገፍ ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ዜጎችና የንግድ ማህበረሰብ አካላት ኤሌክትሮኒካዊ የአገልግሎት መጠየቂያ ዕቅዶችን በመሙላትና አስፈላጊ ሰነዶችን ስካን አድርጎ በማያያዝ ከየትኛውም ቦታና ጊዜ የአገልግሎት ጥያቄያቸውን ማቅረብ ይችላሉ፡፡ ከዚህም በላይ የአገልግሎት ሂደት መከታተያ ልዩ ቁጥርን በመጠቀም የጠየቁት አገልግሎት የደረሰበትን ሂደት መከታተል
፣ በአካል መቅረብ በሚያስፈልግበት ወቅት የቀጠሮ ቀን መያዝ፣ ወቅታዊ መልዕክቶችን በኢ-ሜይል እና በአጭር የፅሑፍ መልዕክት መቀበል፣ እንዲሁም ለቀጣዩ አገልግሎት አሰጣጥ ጠቃሚ የሆኑ አስተያየቶችን ለመስጠት ይችላሉ።


እነዚህን የኤሌክትሮኒካዊ አገልግሎቶች ጠቀሜታ በመረዳት፣ የመገናኛና የመረጃ ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከግብርና ሚኒስቴር፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከከተማ ልማት እና ኮንስራክሽን ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ የምግብ፤ የመድሃኒትና ጤና እንክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን፣ የተወጣጣ ከ28 በላይ ትራንዛክሽናል አገልግሎቶችን ተግባራዊ አድርጓል።
 

ኤሌክትሮኒካል አገልግሎቶች የሚሰጡ መንግስታዊ ተቋማት ለመመልከት ይህንን ይጫኑ።

በኤሌክትሮኒክስ የቀረቡ የህዝብ አገልግሎቶችን ለመመልከት ይህንን ይጫኑ።


የአመለካከት መለኪያ ዳሰሳ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሮኒካዊ ግልጋሎት ተጠቅመው ያውቃሉ?
ምላሾን ያስገቡ  ውጤቱን ይመልከቱ

                                                                                                   © የቅጅ መብት 2005 የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር.